ወደ ዋናው ይዘት ይለፉ
ጠበቃ ያነጋግሩ

Proactive Prevention. Effective Solutions.

ሙግት ከመነሳቱ በፊት እንሰራለን።

የህግ ችግሮች ወደ ሙግት ከማምራታቸው በፊት ተግባራዊ መፍትሄ ሊሰጣቸው ይገባል። የፍትህ ቀዳሚ ዓላማ ችግርን አስቀድሞ መከላከል ነው፤ የNexus አሰራርም የተመሰረተው በዚሁ መርህ ላይ ነው።

የህግ ችግርን የሚፈቱባቸው ሁለት መንገዶች

ከሙግት በኋላ

ተለምዷዊው አሰራር ብዙውን ጊዜ ትኩረት የሚያደርገው ሙግት ከተነሳ በኋላ ጉዳዩን በፍርድ ቤት ክስ መፍታት ላይ ነው።

ከሙግት በፊት

Nexus ሙግት ከመነሳቱ በፊት በመስራት፣ ደንበኞች የህግ ስጋቶችን እንዲለዩ፣ መፍትሄ እንዲያገኙ እንዲሁም ህጋዊና የንግድ ጥቅሞቻቸውን እንዲያስጠብቁ ያግዛል።

የስያሜው ትርጉም

Nexus ማለት በሁለት ነገሮች መካከል ያለ ግንኙነት ወይም ትስስር ማለት ነው። Nexus ህግ፣ ቅድመ መከላከል እና ተግባራዊ መፍትሄዎች የሚገናኙበት ማዕከል ሆኖ ያገለግላል።

The Nexus symbol: an N cut in two by a green compass needle
  • የ N ፊደል ግራ ክፍል ቅድመ መከላከልን ይወክላል።
  • የቀኝ ክፍሉ ደግሞ መፍትሄዎችን ይወክላል።
  • ሁለቱን የሚያስተሳስረው መርፌ Nexus ነው።

ተደጋጋሚ ጥያቄዎች

Nexus Legal Solutions ምን ይሰራል?
Nexus Legal Solutions LLP በአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ የሚገኝ የንግድ ህግ ድርጅት ነው። የምንሰራው ሙግት ከመነሳቱ በፊት ነው፤ ደንበኞች የህግ ስጋቶችን እንዲለዩ፣ ተግባራዊ መፍትሄ እንዲያገኙ እና ህጋዊና የንግድ ጥቅሞቻቸውን እንዲያስጠብቁ እናግዛለን። ሙግት ማስቀረት በማይቻልበት ጊዜ ደግሞ የፍርድ ቤት ሙግቶችን እንይዛለን።
የቅድመ መከላከል የህግ አገልግሎት ምንድን ነው?
የቅድመ መከላከል የህግ አገልግሎት ማለት አንድ የህግ ችግር ወደ ሙግት ከማምራቱ በፊት እልባት መስጠት ማለት ነው፤ ይህም ስጋቶችን መለየትን፣ ችግሮችን አስቀድሞ መፍታትን እና አላስፈላጊ የፍርድ ቤት ሙግትን ማስቀረትን ያካትታል።
የምታገለግሏቸው እነማንን ነው?
የውጭ እና የአገር ውስጥ ባለሀብቶችን፣ ኩባንያዎችን፣ የውጭ ዜጎችን፣ የንግድ ተቋማትን እና ግለሰቦችን።
ምን ዓይነት አገልግሎቶችን ትሰጣላችሁ?
የንግድ ድርጅቶች የህግ ምክር አገልግሎት፤ ድርጅት ማቋቋምና ማዋቀር፣ የኮርፖሬት አስተዳደር፤ የውል አስተዳደር፣ የንግድ ስምምነቶች፤ የህግ ማጣራት፣ የህግ ተገዢነት፤ የአሰሪና ሰራተኛ ህግ አገልግሎት፤ የህግ ስጋት አስተዳደር፤ የድርድር እና የግብይት ድጋፍ፤ ሙግት መከላከል እና ከክስ በፊት የሚደረግ ሂደት፤ የንግድ ድርጅቶች ሰነድ ዝግጅት፣ ኢንቨስትመንት እና የሽርክና ማህበር፤ M&A፣ የንግድ ግብይቶች፤ እንዲሁም የፍርድ ቤት ሙግት።
ቢሯችሁ የት ይገኛል?
ሠንጋ ተራ ነጋዴዎች ህብረት አ.ማ. ህንፃ፣ 19ኛ ፎቅ፣ ቢሮ 19B005፣ ልደታ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 07፣ አዲስ አበባ።
የስራ ሰዓታችሁ መቼ ነው?
ከሰኞ እስከ ቅዳሜ፣ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 6:30 እና ከቀኑ 7:30 እስከ 11:30 (ዓለም አቀፍ ሰዓት፡ 8:30 እስከ 12:30 እና 1:30 እስከ 5:30)።
ጠበቃ እንዴት ማነጋገር እችላለሁ?
በስራ ሰዓት በ +251 992 611 919 ይደውሉ፣ ወይም በአካል ወደ ቢሯችን ይምጡ።

ጠበቃ ያነጋግሩ።

ያጋጠመዎትን ሁኔታ ያስረዱን፤ የህግ ስጋቱ የት እንዳለ እንጠቁምዎታለን።

ሙሉ የአድራሻ ዝርዝር
+251 992 611 919

ከሰኞ እስከ ቅዳሜ፣ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 6:30 እና ከቀኑ 7:30 እስከ 11:30 (ዓለም አቀፍ ሰዓት፡ 8:30 እስከ 12:30 እና 1:30 እስከ 5:30)